የእስራኤል አክራሪ ወግ አጥባቂዎች ከ2.3 ሚሊዮኑ ፍልስጤማውያን ብዙዎቹ ጋዛን ለቀው እንዲወጡ የሚያደርገውን የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕን እቅድ በደስታ ተቀብለዋል። “ስደትን ማበረታታት ዓለም አቀፍ ሕግን አይጥስም” ይላሉ። ፍልስጤማውያን ግን እቅዱን ውድቅ አድርገውታል።
የእስራኤሉ የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው እንዲወጡ ለማበረታታት በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ "የፍልሰት ባለሥልጣን" እያቋቋሙ መኾኑን ተናግረዋል።
ቤዛሌል ስሞትሪች፣ የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር “ስደትን ለማበረታታት የምናወጣው እያንዳንዱ ብር፣ ደጋግመን በመታገል ከምንከፍለው ዋጋ ያነሰ ነው። በጀቱ ለዚህ እቅድ እንቅፋት አይሆንም፣ ይህ ሌላ እቅድ ብቻ አይደለም። በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስራኤል ታሪካዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል አቅም ነው" ብለዋል።
የኬኔሴት አባል የሆኑት ሲምቻ ሮትማን ይህ "ወደሌላ ቦታ የማዛወር" እቅድ በቅርቡ በግብጽ እና በአረብ ሊግ ከቀረበው እቅድ የበለጠ ተጨባጭ ነው፣ የእነሱ እቅድ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በአሸባሪነት የፈረጀችው ሐማስ ትጥቅ ሳይፈታ የፍልስጤም አስተዳደር፣ ጋዛን እንዲመራ ያስችለዋል።” ይላሉ።