የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ ዐርብ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ እስካሁን 246 ኢትዮጵያውያን ከሚያንማር ታይላንድ መግባታቸውን ገልጸው፣ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ከሕንድ ኒውዴልሂ የልዑካን ቡድን ተልኮ ከታይላንድ ኢትዮጵያውያኑን መመለስ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
ከሚያንማር ወደ ታይላንድ ተመልሰው በካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም፣ መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው በጉጉት በመጠባበቅ ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል። ከአጋቾች እጅ ነጻ ወጥተው በሚያንማር ወታደራዊ ካምፕ እንደሚገኙ የነገሩን ደግሞ ወደ ታይላንድ መሻገርን በተስፋ እየተጠባበቁ እንደኾነ ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም