በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾኑ


አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ እየተካሔደ ባለው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኮሚሽኑን በቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ የተመረጡት፣ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ።
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ እየተካሔደ ባለው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኮሚሽኑን በቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ የተመረጡት፣ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ።

ጅቡቲን ለብዙ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ ቀጣዩ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመረጡ። ‘

አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤት እየተካሔደ ባለው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ፣ መሪዎቹ በሚስጥር በሰጡት ድምጽ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ኮሚሽኑን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ኮሚሽኑን እንዲመሩ በሊቀመንበርነት የተመረጡት የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሔደውና ብርቱ ፉክክር በታየበት፣ እንዲኹም እስከ ሰባተኛ ዙር ድረስ በዘለቀ ምርጫ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ አግኝተው ነው።

ከሳምንት በፊት 60ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት ዩሱፍ፣ በምርጫው አሸናፊ የኾኑት የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ነው።

ዩሱፍ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዙሮች በ18 እና በ19 ድምፅ አግኝተው ከራኢላ ጋራ በተቀራረበ ሁኔታ ሁለተኛ ዙር ላይ ነበሩ። ከሦስተኛው ዙር ጀምሮ በተካሔዱት የድምጽ አሰጣቶች ግን ዩሱፍ በመሪነት ቀጥለዋል። በመጨረሻም ለአሸናፊት የሚያበቃው 33 ድምጽ በማግኘት የመሪነቱ ቦታ ተረክበዋል።

አዲሱ የኅብረቱ ተመራጭ ኮሚሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር፣ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው አገልግለዋል። በአፍሪካ አህጉር ረዥም ጊዜ ያገለገሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ናቸው።

ከኅብረቱ ከታገዱት ስድስት ሀገራት በስተቀር 55ቱም የአባል ሀገራት በ38ኛው የኅብረቱ መሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጭ ለቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት እንደተናገሩት፣ 29 ፕሬዝዳንቶች ፣ ሦስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና አንድ ንጉስ በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል። ከአፍሪካ ኅብረት አባልነት የታገዱት ስድስቱ ሀገራት ቡርኪናፋሶ፣ጋቦን፣ጊኒ፣ማሊ፣ኒጀር እና ሱዳን ናቸው።

የዘንድሮው የመሪዎች ጉባኤ በመካሔድ ላይ የሚገኘው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት አማጽያን በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍሎች እየገሰገሱ ባሉበት ወቅት ነው። የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች አስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል።

መሪዎቹ ሊወያዩበት ያቀዱት ሌላው የግጭቱ ዋና ማዕከል ሱዳን ናት። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ እና የሰብአዊ አገልግሎት ሠራተኞች እና ሲቪሎችን ደኅንነት እንዲጠብዙ ጥሪ አቅርበዋል። ጉቴሬዥ 26 ሚሊዮን ለሚጠጉ አስቸኳይ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሱዳናውያን ዜጎች 6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG