በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የኾነው ጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ፣ በየዓመቱ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች ለመጡ ተማሪዎች መርሐ ግብሩን ያዘጋጃል፡፡በዘንድሮው መርሐ ግብር፣ 45 ኢትዮጵያውያን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
የመርሐ ግብሩ አስተባባሪ፣ በትምህርት ላይ የሚሠራው "ኦል ፋውንዴሽን" ሲኾን፣ የተቋሙ መሥራች እና የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ኑርሑሴን ሐሰን ሑሴን፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡