በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕና ኢሺባ ለአሜሪካና ጃፓን “አዲስ ወርቃማ ዘመን” መጥቷል አሉ


የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረፕም እና የጃፓኑ ጠቅላይ ምኒስትር ሺጌሩ ኢሺባ በዋይት ሃውስ (ፎቶ ኤፒ የካቲት 7፣ 2025)
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረፕም እና የጃፓኑ ጠቅላይ ምኒስትር ሺጌሩ ኢሺባ በዋይት ሃውስ (ፎቶ ኤፒ የካቲት 7፣ 2025)

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረፕም እና የጃፓኑ ጠቅላይ ምኒስትር ሺጌሩ ኢሺባ ትላንት በዋይት ሃውስ ተገናኝተው፣ ለአሜሪካና ጃፓን “አዲስ ወርቃማ ዘመን” መጥቷል ሲሉ አውጀዋል።

የሺጌሩ ኢሺባ ጉብኝት የመጣው ዶናልድ ትረምፕ በውጪ ጉዳይ ፖሊሲ መስክ ሰሞኑን ሲናገሯቸው የነበሩት ጉዳዮች አጋሮችንም ሆነ ባላንጣዎችን በሚያሳስብበት ወቅት ነው።

በጃፓን አብዛኞች ጠቅላይ ምኒስትሩ በአሜሪካ ዶናልድ ትረምፕን ለማግኝት ጉብኝት ማድረጋቸው አስጨንቋቸው ነበር ያለው የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ሃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ዘገባ፣ ኋላ ላይ ግን ጠቅላይ ምኒስትሩ በውይይቱ መልካም ውጤት ማሳይታቸውን ጠቁሟል።

“እንደ ጠቅላይ ምኒስትሩ መልከ መልካም ብሆን እመኝ ነበር፣ ግን አይደለሁም” ሲሉ ዶናልድ ትረምፕ ቀልድ ጣል ሲያደርጉ፣ ሺጌሩ ኢሺባ በበኩላቸው፣ ዶናልድ ትረምፕ ያለፈውን ምርጫ ለማሸነፍና ከግድያ ሙከራ በኋላም ዓላማቸውን ለማሳካት ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ካሉት አጨቃጫቂ ጉዳዮች ውስጥ፣ ‘ኒፖን ስቲል’ የተሰኘውና በፒትስበርግ የሚገኘውን የብረት ማምረቻ ጃፓን በ15 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ያቀረበችው ሃሳብ፣ በቀድሞው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም ሆነ በወቅቱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ተቀባይነት ያለማግኘቱ ይገኝበታል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት የብረት ኢንዱስትሪው ለአሜሪካ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያመለከቱት ዶናልድ ትረምፕ፣ ፋብሪካውን ከመግዛት ይልቅ ሌላ መዋዕለ ነዋይ መድበው እንዲሠሩ ሃሳብ አቅርበዋል።

የጸጥታ ጉዳይን በተመለከተ ሁለቱ ሃገራት በሰሜን ኮሪያ የተደቀነውን የኑክሌር ስጋትና ቻይና በታይዋንም ሆነ በአካባቢው ውቅያኖስ ላይ የደቀነችውን ስጋት በጋራ መመከቱን እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG