በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የሩዋንዳና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች የተኩስ አቁም በሚጠይቀው ጉባኤ ላይ ተገኙ

የሩዋንዳና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች የተኩስ አቁም በሚጠይቀው ጉባኤ ላይ ተገኙ


የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ በዳር ኤስ ሳላም ጉባኤ ላይ ሲሳትፉ (ፎቶ ኤኤፍፒ የካቲት 8፣ 2025)
የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ በዳር ኤስ ሳላም ጉባኤ ላይ ሲሳትፉ (ፎቶ ኤኤፍፒ የካቲት 8፣ 2025)

የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ እና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አቻቸው ፊሊክስ ቺሴኬዲ በታንዛኒያ እየተካሄደ ባለውና የአካባቢው ሃገራት በኮንጎ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በጠየቁበት ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።

በሩዋንዳ የሚደገፉት ኤም 23 አማጺያን በማዕድን ሃብቷ በምትታውቀው ኮንጎ ሠፊ ቦታዎችን በፍጥነት ተቆጣጥረዋል። በግስጋሴው ወቅትም በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታችውን ሲያጡ በርካቶች ትፈናቅለዋል።

ቡድኑ ስልታዊ ጠቀሜታ ያላትን ጎማ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሲቆጣጠር፣ ግስጋሴውን እየቀጠለ መሆኑም ታውቋል።

በዳር ኤስ ሳላም በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ስምንት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሃገራት ተወካዮችና 16 የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ አባላት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ፖል ካጋሜ በጉባኤው ላይ በአካል ሲገኙ፣ ቺሴኬዲ ደግሞ በቪዲዮ አማካይነት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

“ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ እናደርጋለን። በተለይም የኤም 23 አማጺያን ግስጋሴያቸውን እንዲያቆሙ፣ የኮንጎ ሠራዊት ደግሞ የበቀል እርምጃዎችን ከመውሰድ እንዲቆጠብ ጥሪ እናደርጋለን” ብለዋል የወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር የሆኑት የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG