በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ የእስልምና አክራሪዎች ሳይፈጽሙት አልቀረም በተባለ ጥቃት 32 ሰዎች ተገደሉ


የማሊ ወታደሮች በእንቅስቃሴ ላይ (ፎቶ ፋይል፣ ቪኦኤ)
የማሊ ወታደሮች በእንቅስቃሴ ላይ (ፎቶ ፋይል፣ ቪኦኤ)

በማሊ በወታደራዊ አጀብ ይጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በእስልምና አክራሪዎች ሳይፈጸም አልቀርም በተባለ ጥቃት 32 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀል።

ተጓዦቹ በሃገሪቱ ወታደሮችና በሩሲያው ቅጥር ወታደሮች ወይም ዋግነር ቡድን አጃቢነት ይንቀሳቀሱ እንደነበርና፣ በሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ወደሚገኝ አንድ የወርቅ ማዕድን በመሄድ ላይ ይነበሩ የውጪ ሃገራት ዜጎችም የሚገኙበት እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ማሊ በአፍሪካ ካሉ ከፍተኛ የወርቅ አምራች ሃገራት አንዷ ብትሆንም፣ ምርቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመናምኗል፡፡

ሲቪሎች ይጓዙበት የነበረውን አጀብ ጂሃድስቶች አድፍጠው ጥቃት እንደከፈቱበት አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል። በጥቃቱ ወታደሮችም እንደሞቱ ታውቋል። በ10 ወታደራዊ መኪኖች የታጀቡ 22 አነሰተኛ አውቶብሶች እንደነበሩም ታውቋል።

አል ቃይዳ፣ እስላማዊ መንግሥት እና ሌሎች ወሮበሎች ማሊን ከአሥር አመታት በላይ ሲያብጡ ከርመዋል። እስላማዊ መንግሥት ለጥቃቱ ኃላፊነት አልወሰደም።

አንድ ክፍተኛ የእስላማዊ መንግሥት ቡድን መሪን መያዙንና በርካታ ጂሃዲስቶችን መግደሉን የማሊ ሠራዊት ባለፈው ወር አስታውቆ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG