በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤልና ሐማስ ተጨማሪ የታጋቾች እና እስረኞች ልውውጥ አደረጉ


በሐማስ የተለቀቀ የአንድ እስራኤላዊ ታጋች ቤተሰቦችና ወዳጆች ደስታቸውን ሲገልጹ (ፎቶ ኤኤፍፒ የካቲት 8, 2025, ቲል አቪቭ)
በሐማስ የተለቀቀ የአንድ እስራኤላዊ ታጋች ቤተሰቦችና ወዳጆች ደስታቸውን ሲገልጹ (ፎቶ ኤኤፍፒ የካቲት 8, 2025, ቲል አቪቭ)

ሐማስ ተጨማሪ ሶስት እስራኤላዊያንን ሲለቅ፣ እስራኤል 183 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቀቀች።

በተኩስ ማቆም ስምምነቱ መሠረት የተለቀቁት እስራኤላውያን የገረጡና የተዳከሙ መሆናቸው ተዘግቧል። የእስራኤላውያኑ ገርጥቶ መታየት እና ሐማስ በሚልቀቁበት ወቅት ያዘጋጀው ሥነ ሥርዓትና ንግግር እንዲያደርጉ ማስገደዱ፣ በእስራኤል በርካቶችን አስቆጥቷል ተብሏል። ለስድስት ሳምንት የታቀደውን የመጀመሪያ ደርጃ የተኩስ አቁም ስምነት እንዲያራዝሙም በእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ ግፊት እንዲጨምር ያደርጋልም ተብሏል።

ሐማስ እስከ አሁን 13 እስራኤላውያን ታጋቾች እና ሶስት የታይላንድ ሠራተኞችን ሲለቅ፣ እስራኤል ደግሞ በአብዛኛው ፍልስጤማውያን የሆኑ 600 እስረኞችን ለቃለች፡፡ በስድስት ሳምንቱ የመጀመሪው ደረጃ ስምምነት 33 እስራኤላውያን ታጋቾችና በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች እንደሚለቀቁ ይጠበቃል።

የዛሬው ልውውጥ የመጣው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከጋዛ ነዋሪዎች እንዲወጡ ተደርገው ሠርጡን አሜሪካ በባለቤትነት ትያዝ የሚለውን ሃሳባቸውን እየገፉ ባለበት ወቅት ነው።

የትረምፕን ሃሳብ የአሜሪካ አጋሮችም ሆኑ ባላንጣ የሆኑ ሃገራት ሲቃወሙት፣ ቤንጃሚን ኔታንያሁ ግን “ከረዥም ከዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበ አዲስ ሃሳብ” ሲሉ አሞካሽተውታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG