ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄኪኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስክሰዋል።
በአሜሪካ አየር መንገድ የሚተዳደረው አውሮፕላን 60 መንገደኞችን እንደያዘ ሲታወቅ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሶስት ሰዎችን ይዞ ነበር ተብሏል።
የአደጋ ሠራተኞች ይህ ዜና በሚታተምበት ሰዓት ርብርብ ላይ ሲሆኑ፣ ሕይወታቸውን ያጡ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሪፖርቶች አመልክተዋል።
መድረክ / ፎረም