በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ መወያየቱን አስታወቀ


ፋይል - እስክንድር ነጋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:45 0:00

ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በእርሳቸው የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ በአማራ ክልል ተገናኝቶ መነጋገሩን ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል አስታውቀዋል።

ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በእርሳቸው የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ በአማራ ክልል ተገናኝቶ መነጋገሩን ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል አስታውቀዋል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰኘውና በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ የፋኖ ቡድኖች አንዱ መሪ እንደሆኑ የሚገልጹት አቶ እስክንድር ነጋ፣ ከእርሳቸው ቡድን ወገን እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች የተውጣጡ የቴክኒካል ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በስም ባልተጠቀሰ ሥፍራ ውይይት ማድረጋቸውን ከአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

ከዓለም አቀፍ ቡድኑ ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት፣ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)፣ የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች እንደሚገኙበት አቶ እስክንድር አስታውቀዋል።

ስብሰባው የተካሂደው ከእነዚሁ ዓለም አቀፍ ተወካዮች ጋራ ከአንድ ወር በፊት የተደረገን የስልክ ውይይት ተከትሎ እንደሆነ አቶ እስክንድር ጠቁመዋል።

“ይህ በቴክኒካል ቡድኖች መካከል የተካሄደ ስብሰባ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ስብሰባ ነው ያደረግነው። የተወያየነውም በሃገሪቱ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መገናኘትና መነጋገር በምንችልበት ላይ ነው።”

የውይይቱ ርዕሶች ምን እንደነበሩ የተጠየቁት አቶ እስክንድር፣ ከዓለም አቀፍ ቡድኑ ጋራ ለመተዋወቅ የተደረገና ቡድናቸው በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አቋም ለመግልጽ የተፈጠረ ዕድል እንደነበር ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህምድ ባለፈው ወር ሲናገሩ፣ አማጺ ቡድኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል። “ለአንድ ሺሕ ዓመት ብትዋጉንም፣ አታሸንፉንም፣ ስለዚህ ወደ ሰላም ኑ” ሲሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ መናገራቸውም ይታወሳል።

ከፌዴራል መንግሥት ጋራ መደራደር የሚለው ጉዳይ በውይይቱ ወቅት እንዳልተነሳም አቶ እስክንድር ገልጸዋል።

“ይህ ጉዳይ አልተነሳም” ያሉት አቶ እስክንድር “እናም ጉዳዩ ሳይነሳ መልስ መስጠት አልችልም። ይህ እኔ የምወስነው ጉዳይ አይደለም። ይህ በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ የሚወሰን ነው። ጥያቄው ሲመጣ፣ ወደ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እወስደዋለሁ። እናም ሥራ አስፈጻሚው ምን እንደሚል እናያለን።” ብለዋል።

መንግሥት በሃገሪቱ የሚገኙ ታጣቂዎችን በትኖ በፌዴራል መንግሥቱ ኅይል ሥር ለማካተትና ወደ ማኅበረሰቡ መልሰው እንዲቀላቀሉ ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ፣ በፋኖ ታጣቂዎችና በፌዴራል መንግሥት ኅይሎች መካከል በሚያዚያ 2015 ግጭት ተቀስቅሷል። በዛው ዓመት ነሐሴ ላይ መንግሥት 23 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በሚኖርበት በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል።

የአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ኅብረት፣ ኢጋድ፣ የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም ኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል። አስተያየታቸው እንደደረሰን እናቀርባለን።

XS
SM
MD
LG