በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሄይቲ መሪ የትራምፕ አስተዳደር ስደተኞችን የመመለስ ዕቅድ አስከፊ ይሆናል አሉ


የሄይቲ የሽግግር ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ሌስሊ ቮልቴር ፤ በቫቲካን፤ ጥር 18/2017 ዓ.ም
የሄይቲ የሽግግር ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ሌስሊ ቮልቴር ፤ በቫቲካን፤ ጥር 18/2017 ዓ.ም

የሄይቲ የሽግግር ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፤ የትራምፕ አስተዳደር የእርዳታ መርሃግብሮችን ለማገድ መወሰኑ፤ ስደተኞችን ወደ መጡበት መመለሱ እና አዳዲስ ስደተኞችን ለመቀበል አለመፈለጉ ለሄይቲ “አደጋ” ይሆናል አሉ።

የሄይቲ የሽግግር ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ሌስሊ ቮልቴር በቫቲካን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ጋር በመገናኘት አቡኑ ሀገራቸውን እንዲደግፉ ጠይቀዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ አስተያየትም ከሊቀ ጳጳሱ ጋር ከተገናኙ በኋላ ከአሶሼትድ ፕሬስ በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት እንደሆነ የዜና አውታሩ ዘግቧል።

የሽግግር ፕሬዝዳንቱ አክለውም "ሄይቲን የሚወዱ ሰዎችን በሮች እያንኳኳሁ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ፤ ሄቲን ይወዳሉ፤ ሀገሪቷን ለመርዳት ዝግጁ ናቸው" ብለዋል ።

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም “በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው፤ በየሳምንቱ የቡድን ግጭት ፈጣሪዎች ህዝቡን እያሸበሩ ነው፤ ይሁን እንጂ ትራምፕ ሄይቲን ቆሻሻ ሀገር ናት ብለዋል፤ ስለዚህ ስለ ሄይቲ የሚገዳቸው አይመስለኝም፤” በማለት ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀደመው የአስተዳደር ዘመናቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከሄይቲ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን መቀበሏን በተመለከተ ተገቢ ያልሆነ ቋንቋ ተጠቅመዋል። በወቅቱ ዋይት ኃውስ ንግግራቸውን ባይስተባብልም፤ ነገር ግን ትራምፕ "ለማኅብረተሰባችን አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ የሚችሉ" ስደተኞች ለመቀበል የሚረዱ የስደተኛ ፖሊሲዎችን ይደግፋሉ በማለት መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG