በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ፍርድ ቤት ቀረቡ


 የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮል ደጋፊዎቻቸው
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮል ደጋፊዎቻቸው

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮል ዛሬ ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፕሬዝዳንቱ የወታደራዊ አስተዳደር ዐዋጅ ለመደንገግ ባደረጉት ሙከራ ጉዳይ ምርመራው የቀጠለ ሲሆን ችሎቱ በቁጥጥር ሥር መቆየት ይኖርባቸው እንደሆን ውሳኔ ይሰጣል።

ሲቪላዊውን አስተዳደር በወታደራዊ አዋጅ ለመሻር ባደረጉት ሙከራ ሀገሪቱን ለትርምስ የዳረጓት ፕሬዝደንቱ በፖሊስ ታጅበው ሲደርሱ ፍርድ ቤቱ ደጃፍ የጠበቋቸው ደጋፊዎቻቸው ከፖሊሶች ጋር ተጋጭተዋል።

መርማሪዎች ፕሬዝደንቱ በእስር የሚቆዩበት ጊዜ እንዲራዘም ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ትላንት ዓርብ ፍርድ ቤቱን የጠየቁ ሲሆን በቀረበው ጥያቄ ላይ ዳኛው ዛሬ ወይም ነገ ውሳኔ እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

ፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንቱ ታስረው እንዲቆዩ ይፈቅዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የእስር ጊዜውን በሃያ ቀን ሊያራዝመው እንደሚችል ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG