በ2017 ዓ.ም. መባቻ ላይ በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሩዋንዳ፣ በዓይነቱ ለየት ያለና ገዳይ የኾነ በቫይረስ የሚተላለፍ ማርበርግ የተሰኘ ወርርሽኝ መገኘቱን አገሪቱ ይፋ አደረገች።
አገሪቱ በወቅቱ የሕክምና ባለሞያዎችን ጨምሮ በበሽታው የተጠቁ ዜጎቿን ብታጣም፣ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ግን የበሽታውን ስርጭት መቆጣጠር ችላለች።
ኪጋሊ በሚገኘው በሩዋንዳ ዩኒቨርሲቲ የድንገተኛ ሕክምና ሳይንስ ክፍል ባልደረባ እና ኒውዮርክ በሚገኘው ሮናልድ ኦ ፕሬልማን ዩኒቨርሲቲ መምህርት የኾነችው ዶር. ጽዮን ፍሬው፣ በወቅቱ በሕክምና ሒደቱ ላይ ከተሳተፉ ሐኪሞች መካከል አንዷ ነበረች።
ማርበርግ፣ አብረዋት የሠሩ ባልደረቦችዋን ሕይወት መቅጠፉንና በሰዓቱ በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ ከመኾኑ የተነሳም ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ከሕፃናት ልጆቿ መነጠል እንደነበረባት አውስታለች።
ከዶር. ጽዮን ጋራ የተደረገውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም