የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ትላንት ረቡዕ ምሽት ከቢሯቸው ኾነው ባደረጉት የመሰናበቻ ንግግር፣ ሥልጣንና ሀብት በተወሰኑ ሰዎች ቁጥጥር ሥር የመኾኑን አደጋ በአጽንዖት አንሥተዋል።
የባይደን ንግግር፣ የዐሥርት ዓመታት የፖለቲካ ጉዟቸውንና የአራት ዓመት የፕሬዝዳንታዊ ሥልጣን ዘመናቸውን መቋጫም ያመላከተ ነበር።
በአንጻሩ፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ቃል መሐላ ፈጽመው ለሁለተኛ ጊዜ አስተዳደሩን ይረከባሉ።
የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ቢሮ ሓላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።