በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በድርድር ለመፍታት፣ በክልሉ የጸጥታ አመራር አካላት ለወራት የተካሔደው ጥረት እንዳልተሳካ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።
ምክትል ፕሬዝደንቱ ትላንት እሑድ ለክልሉ ብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ በጉባኤ ላይ የተሳተፉትና ያልተሳተፉት በሚል የለዩዋቸው ሁለቱ የተከፋፈሉት የህወሓት አመራሮች፣ሁለቱም አሸናፊ የሚኾኑበትን መንገድ ከመምረጥ ይልቅ አንደኛው አንደኛውን ለማጥፋት በመፈለጋቸው ድርድሩ ሊሳካ አልቻለም ብለዋል። ከሁለቱም ወገን ምላሽ ለማግነት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
/መግለጫውን በተመለከተ የተሰናዳውን ዝርዝር ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
መድረክ / ፎረም