በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን የገናን በዓል በተለያየ ድባብ ውስጥ ለመቀበል እየተሰናዱ ነው


 ኢትዮጵያውያን የገናን በዓል በተለያየ ድባብ ውስጥ ለመቀበል እየተሰናዱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:18 0:00

ገናን ለመቀበል በበዓል ግብይት ላይ ያገኘናቸው አስተያየት ሰጪዎች፣ አንዳንድ የበዓል ፍጆታ ምርቶች ተመጣጣኝ ዋጋ ሲኖራቸው ገሚሱ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ አስተያየታቸውን የሰጡን ሸማቾች እና ነጋዴዎች እንዳሉት፣ ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁኔታ በተለየ መልኩ መንገዶች በአብዛኛው ክፍት በመኾናቸው ምርቶች በበቂ ደረጃ ገብተዋል። ኾኖም፣ የማኅበረሰቡ የመግዛት አቅም ውስንነት ግብይቱን እንዳቀዛቀዘው ገልጸዋል፡፡ ብዙዎች እንደየአቅማቸው ለበዓሉ ሲሰናዱ፣ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ደግሞ፣ “በዓሉን ለማክበር የሚያስችል ኹኔታ ውስጥ አይደለንም” ይላሉ። ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG