በናይጄሪያ የገና ስጦታ በማከፋፈል ላይ በነበሩ በሁለት በጎ አድራጎት ዝግጅቶች ላይ በተከሰተ መረጋገጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ13 ወደ 32 ማሻቀቡን የሀገሪቱ ፖሊስ ዛሬ እሁድ አስታውቋል።
በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከከፋ የኑሮ ውድነት ቀውስ ጋር እየታገለች ባለችው ናይጄሪያ የምግብ እርዳታዎችን ለመቀበል ሰዎች በሰፊው ወጥተው የነበረ ሲሆን፤ በትንሹ አራት ህጻናትን ጨምሮ ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል።
ከሟቾቹ 22ቱ በደቡብ ምሥራቅ አናምብራ ግዛት ኦኪጃ ነዋሪዎች ሲሆኑ፤ ትላንት ቅዳሜ አንድ ገባሬ ሰናይ ተቋም በዓሉን በማስመልከት ምግብ ለማከፋፈል ባዘጋጀው መርሃግብር ላይ ጉዳቱ መከሰቱን የአካባቢው ፖሊስ ቃል አቀባይ ቶቹቹኩ ኢኬንጋ ተናግረዋል።
በአቡጃ ከተማ የነበረውን ተመሳሳይ ክስተት ያዩ የዓይን ምስክሮች ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፤ በቤተክርስቲያኑ በር ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መርሃግብሩ ከመጀመሩ በፊት ቀድመው በመገኘት፤ ከሌሊቱ አስር ሰዓት አንስቶ ወደ ግቢው ለመግባት ሲጥሩ ነበር ብለዋል።
ክስተቱ ከቀናት በፊት በርካታ ህጻናት የሞቱበትን ሌላ ተመሳሳይ ሁኔታ የተከተለ ሲሆን፤ የናይጄሪያ ፖሊስ በሁለቱ ጉዳዮች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
መድረክ / ፎረም