በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በጋዛ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎች ሞቱ


ጋዛ ታህሳስ 13/ 2017 ዓ.ም
ጋዛ ታህሳስ 13/ 2017 ዓ.ም

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ዛሬ ሌሊት እሁድ ንጋት ላይ ባደረገችው ጥቃት አምስት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 20 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የህክምና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ባለስልጣናት በእየሩሳሌም የካቶሊክ ቤተክርስትያን መሪ የሆኑት ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ጋዛ ገብተው የቅድመ-ገና ቅዳሴን ከግዛቱ አነስተኛ ክርስቲያን ማኅበረሰብ አባላት ጋር እንዲያከብሩ ፈቅደዋል።

በጋዛ ከተማ የተፈናቀሉ ሰዎችን ባስጠለለ አንድ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሦስት ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቋል። በሀማስ ከሚመራው መንግስት ጋር ግንኙነት ያለው ሲቪል መከላከያ ቀደም ብሎ ከተገደሉት መካከል አራት ህጻናት እንደሚገኙበት ተናግሯል።

የእስራኤል ጦር ጥቃቱ በቀጥታ ያነጣጠረው በስፍራው በተጠለሉ የሀማስ ታጣቂዎች ላይ ነው ሲል ተናግሯል።

ስለጥቃቱ እንስካሁን ድረስ ላይ ከሀማስ የተሰጠ አስተያየት የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG