በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣሊያኗ መሪ ጆርጂያ መሎኒ ሩሲያ የጋረጠችው የደህንነት ስጋት እያየለ ነው አሉ


የጣሊያኗ መሪ ጆርጂያ መሎኒ እና የአውሮፓ ኅበረት ሃላፊዎች በፊንላንድ ታህሳስ 2017 ዓ.ም
የጣሊያኗ መሪ ጆርጂያ መሎኒ እና የአውሮፓ ኅበረት ሃላፊዎች በፊንላንድ ታህሳስ 2017 ዓ.ም

የጣሊያኗ መሪ ጆርጂያ መሎኒ ሞስኮ ህገ-ወጥ ስደትን እና ሌሎች ጉዳዮችን በመጠቀም የአውሮፓ ኅብረትን ለመናድ፤ ከፍተኛ የሆነ የደህነንት ስጋት ደቅናለች በማለት ተናገሩ።

በፊንላንድ ሰሜን ላፕላንድ አውራጃ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የጣሊያን፣ የስዊድን እና የግሪክ መሪዎች እንዲሁም የአዉሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ የተገናኙ ሲሆን፤ በሰሜን ላፕላንድ አካባቢ፣ በኖርዲክ ክልል እና በሜዲትራኒያን ባህር ደህንነት እንዲሁም በደቡብ አውሮፓ ስላለው የስደት ጉዳይ ተግዳሮቶች ተወያይተዋል።

ወግ አጥባቂ መንግስት የሚመሩት ጆርጂያ ሜሎኒ ስለ ሩሲያ በጋዜጠኞች የተጠየቁ ሲሆን “አደጋው ከምናስበው በላይ ሰፊ ስጋት የደቀነ መሆኑን መረዳት አለብን” በማለት ተናግረዋል።

ሜሎኒ የዩክሬን ግጭት ከተጠናቀቀ በኋላ በአውሮፓ ኅብረት ደህንነት ላይ ከሩሲያም ሆነ ከሌላ ቦታ የሚከሰተው አደጋ ስለማይቆም ኅብረቱ ለዚህ ዝግጁ መሆን አለበት ሲሉ አሳበዋል።

አያይዘውም “ይህ በጣም ሰፊ የሆነ የደህንነት ሃሳብ መሆኑን ማወቅ አለብን ይሄ በዲሞክራሲያችን፣ በህዝባችን አስተያየት ላይ ተጽዕኖ መፈጠርን እና በአፍሪካ ስለሚሆነው ነገር፣ እንዲሁም ስለ ጥሬ እቃ፣ እና ስደትን በመሳሪያነት መጠቀም ላይ ያተኮረ ነው” በማለት ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ የአውሮፓ ኅብረት ድንበሩን ለመጠበቅ የበለጠ ተግቶ እንዲሰራ እና ሩሲያ ወይም የትኛውም "ወንጀለኛ ድርጅት" የህገወጥ ስደተኞችን ፍልሰት እንዲመራው ሊፈቀድ እንደማይገባ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ ፊንላንድ እና ኢስቶኒያንን ጨምሮ አንዳንድ የኅብረቱ አባላት ከሩሲያ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከሌሎች ሀገራት የሚመጡ ህገወጥ ስደተኞች ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ሳያደርጉ፤ በሩሲያ በኩል ወደ አውሮፓ ኅብረት ግዛቶች እንዲገቡ መፈቀዳቸው የአውሮፓ ኅብረትን ደህንነት እየጎዳ ነው ሲሉ ከሰዋል።

ሞስኮ ሩሲያ ሆን ብላ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት እየገፋች ነው የሚለውን ክስ አስተባብላለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG