በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት ፈረሙ


የአሜሪካን መንግሥትን ከመዘጋት የሚታደገው በጀት የሚጸድቅበት ገደብ ከማለፉ በፊት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ትላንት ታኅሣሥ 20 ዕኩለ ሌሊት ላይ ሴኔቱ በጀቱን ሲያጸድቅ፣ በሴኔት የአብላጫው ፓርቲ የሆነው የዲሞክራቲክ ፓርቲው መሪ ቻክ ሹምር ምክር ቤት ውስጥ ደስታቸውን ሲገልጹ።
የአሜሪካን መንግሥትን ከመዘጋት የሚታደገው በጀት የሚጸድቅበት ገደብ ከማለፉ በፊት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ትላንት ታኅሣሥ 20 ዕኩለ ሌሊት ላይ ሴኔቱ በጀቱን ሲያጸድቅ፣ በሴኔት የአብላጫው ፓርቲ የሆነው የዲሞክራቲክ ፓርቲው መሪ ቻክ ሹምር ምክር ቤት ውስጥ ደስታቸውን ሲገልጹ።

የገና እና ዘመን መለወጫ በዓላት በተቃረቡባት ዩናይትድ ስቴስትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት በሚታደገው የበጀት ሰነድ ላይ ፊርማቸው አኑረዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ዓመታዊ በጀትን ለማጽደቅ ምክር ቤቱ በድርድር ላይ ባለበት ወቅት፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በአቀረቡት የዕዳ ጣሪያን ከፍ የማድረግ ጥያቄ ምክኒያት እስከ ዐርብ እኩለ ሌሊት ድረስ የቆየው የበጀት ጉዳይ ባይደን ቅዳሜ ዕለት ሰነዱ ላይ ባሳረፉት ፊርማቸው ድምዳሜ አግኝቷል።

ባይደን በጀቱ ሕግ ኾኖ እንዲጸድቅ የፈረሙት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት ማጽደቁን ተከትሎ ነው።

የጸደቀው በጀት መንግሥቱን እስከ መጪው መጋቢት አጋማሽ የሚያቆየው በጀት ሲኾን፣ 100 ቢሊዮን ዶላር ለአደጋ ጊዜ ርዳ እንዲኹም 10 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለግብርና ሥራ ለተያያዘ ድጋፍ ይውላል።

በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር ያለው የሕግ መምሪያ ምክር ቤት እና በዲሞክራት አብላጫ ቁጥጥር ስር ያለው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታገደውን በጀት ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ አጽድቀዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የበጀት ረቂቁን እንደሚደግፉና ሕግ እንዲኾን እንደሚፈርሙ ዐርብ ዕለት ተናግረው ነበር። የጸደቀው በጀት የፌደራል መንግሥቱን የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል አያደርግም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG