በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቴክኒክ ችግር ያጋጠመው አውሮፕላን በሰላም ማረፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ/ ከአየር መንገዱ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ/ ከአየር መንገዱ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ

ወደ ዱባይ ሊጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ በአጋጠመው የቴክኒክ ችግር ፣ ወደ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ መመለሱን አየር መንገዱ አስታወቀ።

አየር መንገዱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ በአወጣው አጭር መግለጫ፣ የበረራ ቁጥሩ ET 612 የኾነ አውሮፕላን ታኅሣሥ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ዱባይ ለሚያደርገው በረራ ከአዲስ አበባ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ፣ በአጋጠመው የቴክኒክ ችግር፣ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም ማረፉን አስታውቋል።

መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች ለጥንቃቄ ሲባል በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉን አስታውቋል።

በአፍሪካ ግዙፍ የኾነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ምክኒያት መንገደኞቹ ለደረሰባቸው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

አውሮፕላኑ ስላጋጠመው የቴክኒክ ችግር ጉዳይ እና በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው የነበሩት መንገደኞቹ ቁጥር በአየር መንገዱ መግለጫ ላይ በዝርዝር አልሠፈረም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG