በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትላንቱ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተሰማው ተኩስና የሰሞኑ የሠላም ስምምነት ጥያቄ አስነስቷል


አዲስ አበባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት የተሰማውን ተኩስ በተመለከተ መንግሥት ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ ኢዘማ ጠየቀ። ተኩሱ የተፈፀመው “ወደ ተሃድሶ ሥልጠና በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት ነው” ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ለተፈጠረው ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

የትላንቱ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተሰማው ተኩስና የሰሞኑ የሠላም ስምምነት ጥያቄ አስነስቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተያያዘ፣ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት ለሕዝብ ግልፅ እንዲደረግም ኢዜማ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG