ዛሬ ቅዳሜ በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም በፌስቡክ ገጹ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ኀዳር 28/2017 አስታውቋል።
አገልግሎቱ ለኤሌክትሪክ መቋረጡ ምክንያት የሲስተም ችግር መሆኑንም ባሰፈረው አጭር መግለጫ ጠቁሟል።
"የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።" በማለት ዜጎች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳሰቧል።
ስለጉዳዩ የአሜሪካ ድምጽ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከረ ነው።
መድረክ / ፎረም