ዓለም አቀፉ የፖሊሶች መረብ የሆነው ኢንተርፖል በአፍሪካ ለሁለት ወራት ባካሄደው ግዙፍ ዘመቻ፤ በሳይበር ጥቃት አማካኝነት ሚሊዮኖች ላይ ገንዘብ ጉዳት፣ እንዲሁም በአስር ሺህዎችን በህገወጥ የሰው ዝውውር የጥቃት ሰለባ አድርገዋል ያላቸውን አንድ ሺህ ስድስት ተጠርጣሪዎች ማሰሩን ባለፈው ማክሰኞ አስታውቋል።
'ዘመቻ ሰሬንጌቲ' የተሰኘው ይኸው የአፍሪፖል እንቅስቃሴ ከአፍሪካ ህብረት የፖሊስ ተቋም ጋር በትብብር ከጎርጎርሳውያኑ መስከረም ሁለት እስከ ጥቅምት 31/2014 ድረስ በ19 ሀገራት መካሄዱን አስታውቋል። ዘመቻው የኢሜል ልውውጦችን፣ የተጠለፉ ሰዎችን የዋስትና ገንዘብ መቀበያ ስፍራዎችን፣ የንግድ ኢሜል ልውውጦችን፣ ዲጂታል ማጭበርበሮችን በሙሉ መከታተሉን አስታውቋል።
የኢንተርፖል ዋና ጸሃፊ ቫልዴሲ ኡርኪዛ "ከባለብዙ ደረጃ የግብይት ማጭበርበሮች እስከ የክሬዲት ካርድ ማጭበርበር በኢንዱስትሪ ደረጃ የሳይበር ወንጀሎች መጠን መጨመር እና ውስብስብነት በጣም አሳሳቢ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም