የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በክልሉ ከሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን ጋር የሰላም ስምምነት ውል መዋዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞ የማዕከላዊ ክልል የጦር አዛዥ የሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ ጋር የስምምነት ውል መፈራረማቸውን አስታውቀዋል።
የስምምነቱ ዝርዝር እስካሁን ድረስ ግልጽ ባይደረግም ነገር ሁኔታውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን “በመላው ኦሮሚያ ክልል የቀጠለውን አለመረጋጋት ለማስቆም መነሻ መሰረት ነው” በማለት አውድሰውታል።
በቴሌቪዥን በተላለፈው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር “ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ዓይነት እርምጃዎች” የሚበረታቱ ናቸው በማለት የጃል ሰኚን እርምጃ አድንቀዋል። ጃል ሰኚ በበኩላቸው የሰላም ስምምነቱ የተቀበሉት “የኦሮሞ ህዝቦችን ስቃይ ከተመለከቱ” በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።
ጃል ሰኚ በመስከረም ወር መገባደጃ ላይ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ባዘጋጁት የስልክ ኮንፈረንስ ላይ "በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ነኝ" በማለት ከኦነግ ጠቅላይ የጦር አዛዥ ጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ መለየታቸውን ያስታወቁት።
የኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑት ጂሬኛ ጉደታ ስምምነቱን “ቀልድ” በማለት አጣጥለውት ነበር። ጂሬኛ መንግስት ስምምነት ላይ የደረሰው ቀድሞውንም ከቡድኑ “ከተባረሩ” ግለሰቦች ጋር ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ዓመት በታንዛኒያ ከፊል ራስገዝ በሆነችው ዛንዚባር ያደረጉት ድርድር ያለስምምነት ተፈጽሟል።
መድረክ / ፎረም