ሥነ ምህዳርን በተመለከተ ማህበራዊ ንቃትን ለመፍጠር ፣ ዜጎች ያላቸውን ተያያዥ መብቶች እና ኃላፊነቶች ለማስገንዘብ ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት መካከል አንዱ "የሥርዓተ ምህዳር ፍትህ ኢትዮጵያ" ይሰኛል ።
የአካባቢ ጥበቃን ፣ ሰፋ ሲልም ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ሊተገበሩ በሚገቡ የህግ ተሳትፎች ዙሪያ የሚያማክረው ተቋም ኃላፊ እስከዳር አውግቸው ነው ።
እስከዳርን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤ (COP29) በሚመለከት እንዲሁም ከተቋሙ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦችን ያጋራን ዘንድ እንግዳችን አድርገነዋል ። ፋይሉ ከስር ተያይዟል።