በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋሞ ዞን ውስጥ ታስረው ይገኛሉ የተባሉ ከ80 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ


ጋሞ ዞን ውስጥ ታስረው ይገኛሉ የተባሉ ከ80 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:45 0:00

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ከዜይሴ ብሔረሰብ ቀበሌዎች የልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ ግጭት ታስረው እስር ቤት የቀሩ 80 ሰዎች በፖሊስና በፍርድ ቤት ምልልልስ በመጉላላት ላይ መኾናቸውን የታሳሪ ቤተሰቦችና አንድ የፓርላማ አባል ገለጹ።

ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ማፍረስ” የሚል ክስ መስርቶባቸዋል። የቤተሰብ አባላቱ ግን፣ ግለሰቦቹ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ከመጠየቅ በስተቀር የሠሩት ወንጀል የለም ሲሉ መከራከሪያ አቅርበዋል።

የአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አምሳሉ ሀንኮ፣ በወረዳው ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰረ ሰው የለም፣ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ስለ ጉዳዩ አቤቱታ ቀርቦለት ክትትል በማድረግ ላይ መኾኑን ገልጿል።

XS
SM
MD
LG