የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጸሐፊ ምርጫ በመጪው የካቲት ወር መጀመሪያ ይካሄዳል። በቦታው በተወዳዳሪነት የቀረቡት የቀድሞዉ የሞርሽዬስ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አኒ ገያን፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ የጅቡቲ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው በማገልገል ላይ የሚገኙት መሐሙድ አል ዩሱፍ፣ የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋና የቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድርያ ናቸው። ባለፈዉ ቅዳሜ ምሽት በአዲስ አበባ የይምረጡኝ ዘመቻ የጀመሩት ራይላ ኦዲንጋ በአፍሪካ የሸቀጦችና የሰዎች ነፃ እንቅስቃሴ እንዲኖር እንደሚሠሩ ተናግረዋል። የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ በኅብረቱ ብልሹ ላሉት አሠራር መፍትሄ ላይ እንደሚያተኩሩ ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
ለመጪው የአፍሪካ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ተጀምሯል
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ዲሴምበር 23, 2024
በ2024 ረዥም ጊዜ የቆዩ አንዳንዶቹ ገዢ ፓርቲዎች ሲቀጥሉ፣ ሌሎች ከባድ ሽንፈት ገጥሟቸዋል
-
ዲሴምበር 23, 2024
ስንፈተ ወሲብ በአይቮሪ ኮስት ወንዶች ላይ ያመጣው አሣር ይላል ርእሱ
-
ዲሴምበር 23, 2024
የማላዊ ጋዜጠኞች ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል እውነትን የማጣራት ክህሎት እየተማሩ ነው
-
ዲሴምበር 19, 2024
የካሜሩን ጋዜጠኞች ከመጪው ምርጫ በፊት የተሳሳተ መረጃን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ
-
ዲሴምበር 19, 2024
ሰብአዊ መብቶችን በኪነ-ጥበብ