በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬኒያ ፍርድ ቤት የምክትል ፕሬዝዳንት ምርጫውን አገደ


የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው የኬኒያ ምክትል ሚኒስትር ሪጋቲ ጋቻጉዋ
የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው የኬኒያ ምክትል ሚኒስትር ሪጋቲ ጋቻጉዋ

የኬኒያ ህግ አውጭዎች የሀገሪቱን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓን በከባድ የስነ ምግባርጉድለት እና ፕሬዚዳንቱን በማቃለል ክስ ከስልጣናቸው እንዲነሱ በማድረግ፤ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶለተተኪ ምክትል ፕሬዝዳንት እጩ አድርገው ያቀረቧቸውን በማጽደው ድምጽ ከሰጡ ከአንድ ቀንበኋላ የኬንያ ፍርድ ቤት አዲሱን ምክትል ፕሬዝዳንት አግዷቸዋል።

ሩቶ ምክትል ፕሬዘዳንት ጋቻጉዋ ከስልጣናቸው እንደተነሱ የምክትል ፕሬዝዳንትነቱን ሥልጣንሹመት ለማካሄድ ጊዜ አላጠፉም።

ተተኪ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ተጨማሪ የ ሁለት ሳምንት ጊዜ የነበራቸው ዊሊያም ሩቶ ምርጫለማድረግ ፣ምክትል ፕሬዝዳንት ጋቻጓን እንዲተኩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኪቱሬ ኪንዲኪንበፍጥነት ለእጩነት ያቀረቡ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ የኪንዲኪ ሹመት ያለምንም ድምጸ ተዐቅቦ እና ተቃውሞ በ236 የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ድምጽ ጸድቋል።

ፍርድ ቤቱ አርብ ዕለት በሰጠው ብይን የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጋቻጓ በመተካታቸው ዙሪያ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ያቀረቡት አቤቱታ “የህዝብ ጥቅም ጥያቄዎችን ዙሪያ ጠቃሚየህግ ጥያቄ አስነስቷል” ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG