በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ተቃጣ


በቂሳሪያ በሚገኘው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ተቃጣ ጥቅምት 09/2017
በቂሳሪያ በሚገኘው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ተቃጣ ጥቅምት 09/2017

የኢራኑ መሪ ባለፈው ዓመት በጎሮጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት ሀማስ የፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ዋናየእቅዱ መስራች የሆኑት የሀማሱ መሪ መገደላቸውን ተከትሎ፤ ሀማስ ከእስራኤል ጋር የሚያደርገውንትግል እንደሚቀጥል ቃል በገቡበት ወቅት፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ መኖሪያ ቤትን ዒላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ መክሸፉን የእስራኤል መንግስት ዛሬቅዳሜ ተናግሯል።

በአንጻሩ በጋዛ፣ የሆስፒታል ባለስልጣናት እና የአሶሺየትድ ፕሬስ ዘጋቢ እንደገለፁት እስራኤል በፈጸመቻቸው የተለያዩ ጥቃቶች ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 21 ሰዎች ተገድለዋል።

ዛሬ ቅዳሜ ማለዳ ከሊባኖስ አቅጣጫ የመጣውን የሰው አልባ ድሮን ጥቃት የሚያስጠነቅቁ ድምጾች በእስራኤል በከፍተኛ ሁኔታ ሲጮሁ ነበር ያለው የእስራኤል መንግስት ቃል አቀባይ መግለጫ፤ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በቂሳሪያ በሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት እሳቸውም ሆኑ ባለቤታቸው እንዳልነበሩ አስታውቆ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ብሏል።

በመስከረም ወር የየመን ሁቲ አማፂያን የኔታኒያሁ አይሮፕላን በቴል አቪቭ በሚገኘው ቤን ጉሪዮን አየርማረፊያ ሲያርፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፋቸው ይታወሳል።

የኔታኒያሁ መኖሪያ ቤትን ዒላማ ካደረገው የድሮን ጥቃት በተጨማሪ ቅዳሜ ማለዳ ላይ በሰሜንእስራኤል ከሊባኖስ የተነሱ ወደ 55 የሚጠጉ ዒላማዎች ላይ መተኮሱን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።የተወሰኑት መክነዋል የተባለ ሲሆን፤ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG