በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅና ሱዳን በናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ተቃውሞ አሰሙ


ዓባይ ወንዝ ላይ የተሰራው የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ (ፎቶ ፋይል)
ዓባይ ወንዝ ላይ የተሰራው የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ (ፎቶ ፋይል)

የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ከዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት ገብቷል ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ሁኔታው የናይል ቤተሰቦችን ትስስር ያጠናክራል ሲሉ በኤክስ ገፃቸው አስፍረዋል።

"የትብብር ማዕቀፉ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱ የዓባይን ውኃ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የተደረገው ረጅም ጉዞ ማብቂያ ነው” ብለዋል፡፡

የትብብር ማዕቀፉን ሲቃወሙ የቆዩት ግብፅና ሱዳን በበኩላቸው፣ የተለመዱ አሠራሮችንና አለምአቀፍ ሕግን የሚጥስ ነው በማለት እንደማይቀበሉት ማስታወቃቸውን መንግስታዊው አህራም ድረ ገጽ ዘግቧል።

ከአርብ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ/ም. ጀሞሮ ለሁለት ቀናት በካይሮ ስብሰባ ያካሄዱትና የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን ጨመሮ፣ በሌሎችም ከውሃ አጠቃቀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የተወያዩት ግብፅና ሱዳን ማዕቀፉ፣ እ.አ.አ በ1929 እና በ1959 የተፈረመውን የናይል ውሃ ስምምነት ይጥሳል ብለዋል።

የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት፣ የተለመዱ አሰራሮችን እና አለምአቀፍ ሕጎችን ይጥሳል ሲሉ ግብፅና ሱዳን መግለጻቸውንም ዘገባው አመልክቷል ።

የማዕቀፍ ስምምነቱ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱ እየተነገረ ያለው፣ ከተፋሰሱ አገራት አንዷ የሆነችው ደቡብ ሱዳን ባለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ተቀብላ ማጽደቋን ተከትሎ ነው።

ስምምነቱ ለ11 ዓመታት ከዘለቀ ውይይት በኋላ፣ በ2002 ዓ.ም (በአውሮፓውያኑ 2010) ግንቦት ወር ላይ በኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ ኬንያ ሲፈረም ብሩንዲ በቀጣዩ ዓመት ስድስተኛ ሀገር ሆና መፈረሟ ይታወሳል።

ከነዚህ ሀገራት መካከል ከኬንያ በስተቀር አምስቱ ስምምነቱን በየሀገሮቻቸው ሲያፀድቁ፣ ደቡብ ሱዳን ስድስተኛዋ የስምምነቱ አፅዳቂ ሀገር ሆናለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG