በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ ሚሊየን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ትምህርት እንዲያገኙ የምትጥረው አፍሪካዊት


አንድ ሚሊየን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ትምህርት እንዲያገኙ የምትጥረው አፍሪካዊት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00

በ79ኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ጎን ለጎን ሲካሄዱ ከነበሩ መሰናዶዎች መካከል 'የማትቆመው አፍሪካ' ወይም unstopable Africa አንዱ ነበር። ለሁለት ቀናት በተደረገው ውይይት ትኩረት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ ልህቀት በአፍሪካ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ንግግር ያደርጉት ደግሞ የ አይ አም ዘ ኮድ 'iamtheCODE' መስራች ትውልደ ሴኔጋላዊቷ የጥምር ዜጋ ባለቤት ፈረንሣይ-ብሪታኒያዊቷ ማሪያም ጃም ናት።

ከሴኔጋል በህገወጥ ስደተኝነት የወጣችው ማሪያም ጃም በጎዳና ተዳዳሪነት፣ ሴተኛ አዳሪነት እንዲሁም በቤት ሰራተኝነት ውስጥ ያለፈች ሴት ናት። እራሷን በራሷ ያስተማረችው ማሪያም ኮዲንግ እና የቴክኖሎጂ እውቀት ብዙዎች ሊያድጉበት የሚችሉት ዘርፍ ነው ትላለች። በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ አፍሪካውያን ልጃገረዶች እና ወጣቶች የነጻ ኮዲንግ ስልጠና እንዲያገኙ በመሰረተችው ተቋም አማካኝነት እየሰራች ነው። ኤደን ገረመው ማሪያም ጃምን በመንግስታቱ ጉባኤ ላይ በኒውዮርክ አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

XS
SM
MD
LG