ዛሬ እሁድ በበርሊን በተካሄደው ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች እና በሴቶች ዘርፍ ድል ተቀዳጅተዋል።
ከወንዶች ሚልኬሳ መንገሻ ከሴቶች ትግስት ከተማ አንደኛ ሆነዋል።
ሚልኬሳ ሁለት ሰዓት ከሦስት ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ የወጣውን ሳይርቢያን ከቱት በሦስት ደቂቃ ቀድሟል።
ሚልኬሳ “ለዚህ ስዘጋጅ ነው የከረምኩት፤ ጉዳናው ለጥ ያለ መሆኑን ሳውቅ እንደማሸንፍ እርግጠኛ ነበረኩ” በማለት ለሮይተርስ ዘጋቢዎች ተናግሯል።
“በለንደን ማራቶን ተሳታፊ ነበርኩ" ያለው ሚልኬሳ " በአንዳንድ ምክንያቶች 38ኛው ኪሎሜትር ላይ ጥዬ ለመውጣት በመገደዴ ተጨንቄ ነበር” ሲል አክሏል፡፡
በሌላ በኩል በሴቶች ዘርፍ አንደኛ የወጣችው ትግስት ከተማ ሁለት ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ከ 42 ሰከንዶች በመግባት ስታሸንፍ፣ መስታዎት ፍቅር እና ቦሰና ሙላቴ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።
መድረክ / ፎረም