እስራኤል በሊባኖስ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶችን መፈጸሟን ተከትሎ፤ ሄዝቦላህ ከ100 በላይ ሮኬቶችን በሰሜናዊ እስራኤል ከሃፊያ ከተማ አቅራቢያ አስወነጭፏል። ሁለቱ ወገኖች ለወራት የዘለቀው ውጥረት መባባስ ተከትሎ ወደ ከፍተኛ ጦርነት እየተሸጋገሩ ይመስላል።
ዛሬ እሁድ የተተኮሱት ሮኬቶች በሰሜን እስራኤል ላይ የአየር ወረራ ማስጠንቀቂያ ጥሪዎችን በማስነሳታቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ መጠለያ እንዲገቡ ተደርጓል። የእስራኤል ጦር ሮኬቶቹ ሲቪሎች ወዳሉባቸው አካባቢዎች ነው የተተኮሱት ያለ ሲሆን፤ ጦርነቱ ሊባባስ እንደሚችል አመልክቷል።
በሃይፋ አቅራቢያ በሚገኘው ኪርያት ቢያሊክ በተሰኘ አካባቢ በሚገኝ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ያረፈ አንድ ሮኬት በትንሹ ሦስት ሰዎችን አቁስሎ፣ ህንፃዎችን እና መኪናዎችን አቃጥሏል። የእስራኤሉ ማጌን ዴቪድ ኤዶም የነፍስ አድን አገልግሎት በአጠቃላይ አራት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።
በሌላ በኩል የእስራኤል ሃይሎች በዚህ የአውሮፓዊያኑ ዓመት መግቢያ ላይ ያገዱትን የአልጀዚራ ዜና አውታር የዌስት ባንክን ቢሮ መውረራቸው ታውቋል፡፡
መድረክ / ፎረም