በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ ዜጎቿ ወደ ሶማሊላንድ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች


አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ - የግብፅ ፕሬዚዳንት /ፎቶ ፋይል/
አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ - የግብፅ ፕሬዚዳንት /ፎቶ ፋይል/

በሶማሊያ የሚገኙ የግብጽ ዜጎች እራስ ገዝ መሆኗን ወዳወጀችው ሶማሊላንድ እንዳይጓዙ በሶማሊያ የሚገኘው የግብጽ ኤምባሲ አስጠነቀቀ።

በሞቃዲሾ የሚገኘው የግብፅ የዐረብ ሪፐብሊክ ኤምባሲ መግለጫ ሁሉም የግብፅ ዜጎች የሶማሊያ አካል ወደ ሆነችው ሶማሌ ላንድ ግዛት እንዳይጓዙ አሳስቧል ሲል ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

መግለጫው ዜጎቹን ለማስጠንቀቅ በወሰነው ውሳኔ "በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አለመረጋጋት፤ በደህንነታቸው ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ" እንዳለ ጠቅሷል።

ሶማሊላንድ በቅርቡ “በጎረቤት ሶማሊያ የተሰማራው የግብፅ ጦር ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል” ስትል ተናግራለች። ከሳምንታት በፊት የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢሳ ካያድ ሶማሊላንድ በሃርጌሳ የሚገኘውን የግብጽ የባህል ቤተመጻህፍትን፤ ባደረባት የደህንነት ስጋት ምክንያት ‘ሙሉ ለሙሉ ለመዝጋት’ ወስናለች ሲሉ አስታውቀዋል።

የግብፅ ወታደሮች እስካሁን ድረስ በሶማሊያ አልተሰማሩም። ይሁን እንጂ የሶማሊያ መንግስት ግብፅ ከመጭው የጎርሳዊያኑ ጥር 2025 ጀምሮ በሀገሪቱ ውስጥ ስራ ሊጀምር እየተዘጋጀ ባለው የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ውስጥ ሚና እንድትጫወት ፍላጎት አለው።

ባለፈው ወር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች - አብደልፈታህ ኤል-ሲሲ እና ሀሰን ሼክ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የመከላከያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በሌላ በኩል ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች እስከ መጭው ታህሳስ 2017 ዓ.ም ድረስ ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG