በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩስያ ሚሳኤል ጥቃት ሶስት ሰዎች መገደላቸውን ዩክሬን አስታወቀች


በዩክሬን ዶኔትስክ ግዛት በቅርብ ጊዜ የተገነቡ ምሽጎች፣ መስከረም 10 2017 ዓ.ም.
በዩክሬን ዶኔትስክ ግዛት በቅርብ ጊዜ የተገነቡ ምሽጎች፣ መስከረም 10 2017 ዓ.ም.

በማዕከላዊ ዩክሬን ክሪቪ ሪህ ሌሊቱን በድረሰ የሩስያ የሚሳኤል ጥቃት አንድ የ12 አመት ወንድ ልጅ እና ሁለት አረጋውያን ሴቶች መሞታቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪ ሰርሂ ሊሳክ ዛሬ ቅዳሜ አስታውቀዋል።

"እኩለ ሌሊት ላይ ከተማዋ ባሸለበችበት እንደገና አስፈሪ የጠላት ጥቃት በኪሪቪ ሪህ ላይ ደርሷል " ሲሉ አስተዳዳሪው ሊሳክ በቴሌግራም ላይ በጽፉት መልዕክት ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም ተናግረዋል። በጥቃቱ የተገደሉት ሁለቱ ሴቶች የ75 እና የ79 ዓመት አዛውንት ናቸው። ሊሳክ በተጨማሪም ሁለት ሕንፃዎች መውደማቸውንና 20 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል

በየጊዜው በአየር ድብደባ የምትመታው የክሪቪ ሪህ በሩሲያ በተያዘው ግዛት አቅራቢያ የምትገኝ ብረት የሚመረትባት ከተማ ናት፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG