በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በታጠቁ አካላት የሚካሄዱ የሰዎች እገታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን የመብት ተቋማት ይገልጻሉ፡፡
አሁን ላይ እገታዎች ከሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ባለፈ አማራጭ የገቢ ማስገኛ እየሆኑ መጥተዋል የሚሉት ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ እና የምርጫ ድጋፍ ኢንስቲትዮት የሚሰሩት የፖለቲካል ሳይንስ እና ህግ ባለሙያው ዶ/ር አደም ካሴ ይህም የመንግስት ህግ የማስከበር አቅም እያሽቆለቆለ መምጣቱን ያሳያል ይላሉ፡፡
እገታ የደረሰባቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ገንዘብ ከፍለው ከተለቀቁ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ለስነ ልቦና ጉዳት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም