በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ተኩስ ማቆም እንዲደረግ በዶሃ ጥረቱ ቀጥሏል


ቃጣር መዲና ዶሃ
ቃጣር መዲና ዶሃ

በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግና ጦርነቱ ወደ ቀጠናው እንዳይስፋፋ ለማድረግ ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች በቃጣር መዲና ዶሃ በመምከር ላይ ናቸው።

ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ግብፅ እና ቃጣር የተውጣጡ አደራዳሪዎች ከእስራኤል ልዑክ ጋራ የተገናኙ ሲሆን፣ ሐማስ በንግግሩ ላይ እንደማይገኝ ትላንት ረቡዕ አስታውቋል። ነገር ግን ከንግግሩ በኋላ የሐማስ ተወካዮች ከአሸማጋዮች ጋራ ሊገናኙ እንድሚችሉ ተነግሯል።

ንግግሩ ነገ ዓርብም ሊቀጥል እንደሚችል ዋይት ሃውስ አስታውቋል።

የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ቢሮ ሃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ እና ዳና ዊሊያምስ ዘገባቸውን ልከዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG