በዩናይትድ ስቴትስ፣ በኅዳር ወር በሚካሔደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩት የዴሞክራቲክ ፓርቲው እና የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ ፕሬዚዳንቶች፣ አብረዋቸው የሚወዳደሩትን ዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንቶችን መርጠዋል፡፡ አሁን ጥያቄው፣ አጣማሪ ዕጩዎቻቸው በምርጫው እንዲያሸንፉ ምን ያህል ይረዷቸው ይኾን? የሚለው ነው፡፡
የቪኦኤዋ ቬሮኒካ ኢግሊሲያስ ባልዴራስ፣ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዎች ታሪክ፣ የዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ሚና በመዳሰስ፣ የአሁኖቹ ዕጩዎች ቲም ዎልዝ እና ጄዲ ቫንስ ለየፓርቲዎቻቸው አሸናፊነት ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅኦ የሚያስቃኝ ዘገባ አጠናቅራለች፡፡