በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓስፖርት አሰጣጥ “አድልዎ ይፈጸማል” ሲል የመብት ተሟጋቹ የአገልግሎት ተቋሙን ከሰሰ


በፓስፖርት አሰጣጥ “አድልዎ ይፈጸማል” ሲል የመብት ተሟጋቹ የአገልግሎት ተቋሙን ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:30 0:00

ሂዩማን ራይትስ ፈርስት የተባለ የመብት ተሟጋች ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎትን፣ የትግራይ ተወላጆችን የዜግነት፣ የእኩልነት እና በነጻነት የመዘዋወር ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን በመጣስ ሲከስ፣ ተቋሙ በበኩሉ፣ “በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸም አድልዎ የለም፤” ሲል ክሱን አስተባብሏል፡፡

ፓስፖርት የሚጠይቁ የትግራይ ተወላጆች፣ “የተለየ እንግልት፣ ወከባ እና ማስፈራሪያ እንደሚፈጸምባቸው በምርመራ አረጋግጫለኹ፤” ያለው የመብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ የፓስፖርት አሰጣጥ መመሪያው አጭር እና ግልጽ ቢኾንም፣ “የትግራይ ተወላጆች ግን በሕግ ባልተቀመጠ መስፈርት፣ ተጨማሪ ሰነድ እና መረጃ ይጠየቃሉ፤ ፓስፖርት ማግኘትም አስቸጋሪ ኾኖባቸዋል፤” ይላል። ተቋሙ፣ ችግሩን በጊዜ የማይፈታው ከኾነም፣ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው፣ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ምክትል ዲሬክተር አቶ መብርሂ ብርሀነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ክሱን ያስተባበለው የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደግሞ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋራ ከሚዋሰኑ ክልሎች የሚመጡትን ዜጎች ኹሉ፣ ኢትዮጵያዊነታቸውን ለማጣራት ተጨማሪ መረጃ እንደሚጠይቅ፣ በተቋሙ የፓስፖርት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ አቶ አዳነ ደበበ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ “የዜግነት መረጃን በማጥራቱ ሒደት የሚስተዋሉ ችግሮችንም ለመፍታት እየሠራን ነው፤” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG