በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሔራዊ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ107ነጥብ9 ብር ዋጋ መሸጡን ገለጸ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ዛሬ ባካሔደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ107ነጥብ9 ብር ዋጋ መሸጡን ሲያስታውቅ፣ 27 ባንኮች በጨረታው ላይ መሳተፋቸውን ገልጿል፡፡

ይህ የብሔራዊ ባንክ ርምጃ፣ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ለማረጋጋት የሚወሰድ መኾኑን፣ የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ተንታኝ የኾኑት ሽዋፈራሁ ሽታሁን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዋጋ ንረት ተጽእኖን ለመከላከል ድጎማ ይደረግባቸዋል ከተባሉ የገቢ ምርቶች አንዱ የኾነው የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል መንግሥት አስታውቋል፡፡

ይህ ርምጃ ጠቃሚ ቢኾንም፣ የትራንስፖርት ዘርፉ ተጨማሪ ትኩረቶችንም እንደሚሻ አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:16 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG