የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባች ፣ የእምነት መሪዎች እና የኦሎምፒክ ባለስልጣናት ዛሬ እሁድ ጠዋት በፓሪስ ኖትረዳም ካቴድራል ፊት ለፊት "እምነት እና ስፖርት እንዴት እርስ በርስ መደጋገፍ እንደሚችሉ" ለማሳየት መሰባሰባቸውን ተናገሩ።
የ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ በክርስትና እምነት ላይ የተሳለቀበትን ዝግጅት አቅርቧል የሚል ውዝግብ ቢነሳበትም የዛሬው የእምነት አባቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ስብስብ የስፖርት እና ሰላም ጥምረትን አስፈላጊነት አፅንዖት መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
ሰላምና እረፍት ታይቶበታል በተባለው የአትሌቶች መንደር የቡድሂዝም፣ የክርስትና እምነት፣ የሂንዱይዝም፣ የእስልምና እና የአይሁድ እምነት ተወካዮች ለኦሎምፒክ ተከፋዮቹ መንፈሳዊ ቡራኬና መጽናኛ መስጠታቸውን የአሶሴዬትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል ።
እ.ኤ.አ. በ2024 የተካሄደው የፓሪስ ጨዋታዎች መክፈቻ ላይ በክርስትና እምነት ከሚታወቀው “የመጨረሻው ራት” ምስል ጋር ተያይዞ የቀረበው ትዕይንት ቫቲካንን ጨምሮ ከሀይማኖት ቡድኖች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
የካቶሊክ ጳጳስ ኢማኑኤል ጎቢሊርድ የስብሰባው ዋና መልእክት ሰላም መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በኦሎምፒክ ስፍራ የሚካሄደው የሃይማኖት እና የስፖርት ቤተሰቦች ሰብስብ የተጀመረው በዘመናዊው የኦሎምፒክ መስራች ፒየር ደ ኩበርቲን እኤአ በ1924 በተካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡
መድረክ / ፎረም