በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓሪስ ኦሎምፒክ አሜሪካ በሞሮክ ተሸንፋ ከውድድር ውጭ ሆነች

 የሞሮኮ ተጨዋቾች የወንዶች የሩብ ፍፃሜ የእግር ኳስ ግጥሚያቸውን ካሸነፉ በኋላ ደስታቸውን ሲገልጹ፣ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. (Photo by Paul ELLIS / AFP)
የሞሮኮ ተጨዋቾች የወንዶች የሩብ ፍፃሜ የእግር ኳስ ግጥሚያቸውን ካሸነፉ በኋላ ደስታቸውን ሲገልጹ፣ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. (Photo by Paul ELLIS / AFP)

በፓሪስ ኦሎምፒክ ሩብ ፍጻሜ የወንዶች እግርኳስ ወድድር ሞሮኮን የገጠመው የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ቡድን 4 ለ0 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡

በፓርክ ዴ ፕሪንስ በተካሄደው ጨዋታም ለሞሮኮ ሶፊያን ራሂሚ፣ ኢሊያስ አኮማች፣ አቻራፍ ሃኪሚ እና መህዲ ማኡሁብ ጎሎችን አስቆጥረዋል።

በፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ በሚኖሩ ብዙ ደጋፊዎች ታጅባ እየተጫወተች ያለችው ሞሮኮ የፊታችን ሰኞ በማርሴይ ከጃፓን ከስፔን አሸናፊ ጋር የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

በጨዋታው የተሸነፈችው ዩናይትድ ስቴትስ እአአ በ2000 ከተካሄደው የሲድኒ ኦሎምፒክ በኋላ ሩብ ፍፃሜ ትደርስ የመጀመርያዋ ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG