በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች አስከሬን ፍለጋው መቆሙን ክልሉ አስታወቀ


please wait

No media source currently available

0:00 0:05:37 0:00

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን የመፈለጉን ሥራ፣ ከ10 ቀናት ጥረት በኋላ ትላንት ረቡዕ ማቆሙን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡

የተገኙት አስከሬኖች የቀብር ሥነ ሥርዓት በክብር መፈጸሙን የገለጹት የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሠናይት ሰሎሞን፣ የስድስት ሰዎችን አስከሬን ግን ማግኘት እንዳልተቻለ አመልክተዋል፡፡

የቤተሰቦቻቸውንና የዘመዶቻቸውን አስከሬን ያላገኙ የቀበሌው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ “አስከሬናቸውን እስከናገኝ ፍለጋውን አናቆምም፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG