አሜሪካዊቷ ኬቲ ሌዴኪ ረቡዕ ሀምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በተካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ በ1,500 ሜትር የውሃ ዋና ውድድር (ፍሪስታይል) በበላይነት በማሸነፍ ሰባተኛውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ በአጠቃላይ 12 ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች።
የ27 ዓመቷ ሌዴኪን በመከተል ፈረንሳዊቷ አናስታሲያ ኪርፒቺኒኮቫ የብር ሜዳሊያ ስታገኝ ጀርመናዊቷ ኢዛቤል ጎሴ በተመሳሳይ ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
ሌዴኪ ከዚህ ቀደም ትልቁን ሽልማት ካገኙት አሜሪካውያን ሴቶች ዳራ ቶሬስ፣ ናታሊ ኩሊን እና ጄኒ ቶምፕሰን ጋር በመሰለፍ ከትላልቆቹ የሴት ዋናተኞች ተርታ ተሰልፋለች።
በወንዶቹ የ200 ሜትር የቢራቢሮ ስልት ዋና ውድድር ፈረንሣዊው ሊዮን ማርጋንድ በፓሪስ ጨዋታዎች ሁለተኛ የወርቅ ሜዳሊያውን አሸንፏል።
ማርችናድ ቀደም ሲል በ400 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል
በ100 ሜትር የፍሪስታይል ውድድር ሁለተኛዋ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያዋን ከስዊድን ያገኘችው ሳራ ስጆስትሮም ድል ቀንቷታል።
አሜሪካዊው ዋነተኛ ቶሪ ሁስኬ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሲሆን ከሆንግ ኮንግ ሲኦብሃን ሀግይ በ100 ሜትር የፍሪስታይል ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፏል።
መድረክ / ፎረም