ወጣት አፍሪካውያን መሪዎችን በየዓመቱ የሚያሰባስበው፣ የማንዴላ ዋሺንግተን ጉድኝት ጉባኤ በዋሺንግተን ዲሲ ላይ ተካሒዷል።
ይህ ጉባኤ፣ በልዩ ውድድር ውስጥ አልፈው የተመረጡ ወጣቶች፣ በአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ፣ ለሳምንታት የሚዘልቅ የትምህርት እና አመራር ሥልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ የሚካሔድ የመደምደሚያ መድረክ ነው።
ዘንድሮ 10ኛ ዓመቱን በደፈነው መርሐ ግብር ላይ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች ከኾኑ ሀገራት የመጡ ወደ አንድ ሺሕ ገደማ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ሀብታሙ ሥዩም ከዘንድሮው የጉባኤው ተሳታፊ ኢትዮጵያውያን ጋራ አጭር ቆይታ አድርጓል።