በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት ለደመወዝ ጭማሬ እና ለድጎማዎች ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤት ሊያቀርብ ነው


መንግሥት ለደመወዝ ጭማሬ እና ለድጎማዎች ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤት ሊያቀርብ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:25 0:00

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ኀሙስ ማብራሪያ ይሰጣሉ” - አሕመድ ሽዴ

የዓለም ባንክ፣ ትላንት ማክሰኞ ለኢትዮጵያ በድጋፍ እና በብድር መልክ የፈቀደውን 1ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር ያካተተ ተጨማሪ የበጀት ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ዛሬ አስታውቀዋል፡፡

ተጨማሪው በጀት፣ የዋጋ ንረት ተጽእኖን ለመቀነስ ለሚወሰዱ የደመወዝ ጭማሬ እና ለሌሎች ድጎማዎች እንደሚውልም ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

ምክር ቤቱ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል በተደረሰው የብድር ስምምነት ላይ ውይይት አድርጎ አጽድቆታል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ እሑድ፣ ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንደሚደግፍ ያሳወቀው የዓለም ባንክ ከለቀቀው ገንዘብ ውስጥ በብድር መልክ የተገኘውን 500 ሚሊዮን ዶላር ለማጽደቅ፣ በአፈ ጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ዛሬ ባካሔደው ውይይት ላይ ከምክር ቤት አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነሥተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG