በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሣይ ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ የባቡር መስመሮችን አስተጓጎለ


ተጓዦች በጋሬ ዱ ኖርድ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ሲጠባበቁ፣ ፣ ፓሪስ፣ ፈረንሳይ፣ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Mark Baker)
ተጓዦች በጋሬ ዱ ኖርድ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ሲጠባበቁ፣ ፣ ፓሪስ፣ ፈረንሳይ፣ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Mark Baker)

ፈረንሣይ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ የተከስተው ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሎምፒክ እና የበጋ እረፍት ተጓዦችን ማስተጓጎሉ ተነገረ፡፡

ከባዱ አውሎ ነፋስ በፓሪስ እና ደቡብ ፈረንሳይ እንዲሁም በስዊዘርላንድ መካከል ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸውን የባቡር መስመሮች አስተጓጉሏል፡፡

ቡርገንዲ በተባለችው ደቡባዊ ምስራቅ የፈረንሳይ ግዛት ዋና ከተማ በነፋስ የተገነደሰው ዛፍ፣ ባቡር ላይ በመወደቁ በፓሪስ የሚገኘው ትልቁን የ ጌር ደ ሊዮን ባቡር ጣቢያን ጨምሮ ሁሉንም ባለከፍተኛ ፍጥነት ባቡሮች እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓል።

ባለሥልጣናት የተቋረጡትን የባቡር መስመሮች መልሶ በመጠገን ከጉዞ የተገቱ ተጓዦችን እንደገና ለማንቀሳቀስ ጥረት ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡

ባለፈው ሳምንት ከተከፈተው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በፊት ተስተጓጉለው የነበሩ የባቡር መስመሮች ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት ጀምረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአየር ትንበያ ባለሥልጣናት በትላንትናው እለት በአብዛኞቹ የፈረንሣይ ግዛቶች ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ነጎድጓዳማ ዝናብ እንደሚኖር አስጠንቅቀዋል፡፡

የዓለም ኦሎምፒክ ጨዋታዎች እየተካሄዱባት የምትገኘው የፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ፣ ለሶስት ተከታታይ ቀናት፣ 31 ዲግሪ ሴልሺየስ (88 ዲግሪ ፋራናይት) የሚደርስ ሙቀት እየታየባት መሆኑ ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG