የሃማስ መሪ እስማኤል ሃንዬ ዛሬ ረቡዕ ኢራን ውስጥ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ሃማስ አስታወቀ። የሃማሱ መሪ የተገደሉት የኢራን አዲሱን ፕሬዚዳንት ቃለ መሃላ በሚፈጽሙበት በዓለ ሲመት ለመገኘት ወደዚያው ባመሩበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።
ሃንዬ የተገደሉት በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ውስጥ መሆኑን አማጺው የሃማስ ቡድን በቴሌግራም ማህበራዊ መድረክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ በዛሬ ማለዳው ጥቃት ከሃንዬ የግል ጠባቂዎች መካከል አንዱ መገደሉን አስታውቆ ክስተቱ በምርመራ ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡
እስራኤል ስለሁኔታው ወዲያኑ የሰጠችው አስተያየት የለም። አንድ የቀድሞ የእስራኤል ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ የኢራን ወኪሎች የሆኑት ሃማስና ሂዝቦላ በቤይሩት እና ቴህራን ላይ ሁለቱ ከፍተኛ መሪዎቻቸው ከተገደሉ በኋላ እስራኤል ላይ ሊወስዱት ስለሚችሉ የበቀል እርምጃ ካላፈው ማክሰኞ ጀምሮ ለበርካታ ሰዐታት በማሰላሰል አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው እንደነበር ዛሬ ረቡዕ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም