ህወሓት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት ለሁለተኛ ጊዜ ለምርጫ ቦርድ አመለከተ
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት)፣ ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት ለሁለተኛ ጊዜ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ማስገባቱን የፓርቲው ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። በፓርቲው ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ ከተነጋገሩ በኋላ ደብዳቤውን እንዳስገቡ የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ምላሽ እናገኛለን ብለው እንደሚጠብቁ ለአገር ውስጥ ብዙኀን መገናኛ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከምርጫ ቦርድ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ዲሴምበር 23, 2024
አዳጊ ልጆችን ለውትድርና በመመልመል የዘፈቀደ እስር ፈጽመዋል የተባሉ በሕግ ይጠየቁ ተባለ
-
ዲሴምበር 20, 2024
የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ